ጅማ አባ ጅፋር የአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ ጉዞውን ዛሬ ይጀምራል
አርትስ ስፖርት 18/03/2011
የ2019 አፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታዎች ዛሬ ይጀመራሉ፡፡
በውድድሩ ኢትዮጵያን በመወከል የሚሳተፈው የ2010 ዓ/ም የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊ ጅማ አባ ጅፋር ሲሆን በቅድመ ማጣሪያው ከጅቡቲው አሳስ/ጅቡቲ ቴሌኮም ጋር ይፋለማል፡፡ ጨዋታው በዋና ከተማዋ ጅቡቲ ላይ የሚከናወን ሲሆን ምሽት 2፡00 ላይ ይጫወታል፡፡
ቡድኑ ትናንት ልምምዱን ያደረገ ሲሁን በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ ተገልጧል፡፡
በሌሎች ጨዋታዎች ስታዴ ሴንትራፍሪኬን ከ ስታዴ ማሌን፣ ቮልካኖ ክለብ ዴ ሞሮኒ ከ አፍሪካን ስታርስ፣ ኢል ናስር ከ አል ሂላል ጁባ፣ ኢል ሂላል ከ ጄ.ኬ.ዩ፣ ታውንሽፕ ሮለርስ ከ ባንቱ፣ ኢቲሀድ ራይዲ ዴ ታንጀር ከ ኢሌክት ስፖርት፣ ክለብ ስፖርቲፍ ኮንስታንቲኖይስ ከ ጋምቴል፣ ኤ.ኤስ.ኤፍ.ቢ ከ ኮቶን ስፖርት፣ ሶኒዴፕ ከ ዜስኮ ዩናይትድ፣ ሳኡራ ከ ስፖርቲንግ ክለብ ዴ ጋኞዋ እና ጃራፍ ዴ ዳካር ከ ኮሮኪ ጋር ይጫወታሉ፡፡