Uncategorized

አልሸባብ በሶማሊያ አወዛጋቢው ምሁር የሚባለዉን ግለሰብና ተከታዮቹን ገደለ

አልሸባብ በሶማሊያ አወዛጋቢው ምሁር የሚባለዉን ግለሰብና ተከታዮቹን ገደለ

አርትስ 18/03/2011

ነዋሪነቱን በጋልካዮ ከተማ ያደረገው ሸይክ አብዲወሊ አሊ ከ14 ተከታዮቹ ጋር ባቋቋመው የትምህርት ማእከል ውስጥ ነው በአጥፍቶ ጠፊዎቹ የተገደለው፡፡

አልጀዚራ እንደዘገበው የአልሸባብ ታጣቂወች ተቀጣጣይ ቦንብ የጫነ ተሸከርካሪን በመጠቀም ወደ ማእከሉ በመግባትን ተኩስ በመክፈት  ነው ጥቃቱን ያደረሱት፡፡

አብዲወሊ በአልሸባብ ኢላማ ውስጥ የገባው ሙዚቃና ዳንስን በመጠቀም እስልምናን ለማወደስ አዲስ አስተምህሮ ይዞ በመነሳቱ ነዉ ተብሏል፡፡

አጥፍቶ ጠፊዎቹ ባደረሱት ጥቃት ከተገደሉት 15 ሰዎች በተጨማሪ ሌሎች 10 ግለሰቦች መቁሰላቸውን የሶማሊያ ባለስልጣናትና ፖሊስ አስታውቀዋል፡፡

የአልሸባብ ወታደራዊ ተልእኮ ቃል አቀባይ አብዲያሲስ አቡ ሙሳብ ግን አብዲወሊን ጨምሮ 26 ሰወችን ገድለናል ብሏል፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami