አርትስ 18/03/2011
ውይይቱም ቀጣዪን ምርጫ ነጻና ፍትሃዊ ለማድረግሊወሰዱ ስለሚገባቸው የሪፎርም ስራዎችላይ ያተኮረ ነበር፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩም ከተፎካካሪ ፓርቲዎቹ ጋር በነበራቸዉ ዉይይት መንግስትም ተፎካካሪ ፓርቲዎቸም ለምርጫዉ ነጻና ዲሞክራሲያዊነት የጋራ ኃላፊነታቸዉን ሊወጡ ይገባል ብለዋል፡፡
ጠ/ሚኒስትሩ ለተፎካካሪ ፓርቲዎቹ የምንሰራው ስራ አገራችንን የማያፈርስ መሆን አለበት ብለዋል፡፡ በተጨማሪም የተፎካካሪ ፓርቲዎች ልዩነት ከህዝብና ከአገር በታች በመሆኑ በመወያየት የጋራ ሀሳብ መያዝ ይቻላል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ በሃሳብ መሰባሰብን አፅንኦት በሰጡበት ውይይት ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎቹም ከፓርቲዎች ቁጥር፣ የህገመንግስት ማሻሻያ ሃሳብ ፣ከመጪው ምርጫ በፊት የህግ የበላይነትን ማረጋገጥን በተመለከተ ጥያቄና አስተያየት ሰጥተዋል፡፡