EducationEthiopiaTech

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ከመቶ ሺህ ዶላር በላይ ያወጣበትን የሳተላይት መቆጣጠሪያ ጣቢያ አስመረቀ

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ከመቶ ሺህ ዶላር በላይ ያወጣበትን የሳተላይት መቆጣጠሪያ ጣቢያ አስመረቀ

አርትስ 27/03/2011

 በዩኒቨርስቲው የሚገኘው የስፔስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በትናንትናው ዕለት የሳተላይት መቆጣጠሪያ ጣቢያ ሲያስመርቅ ኢትዮጵያ በህዋ ምርምር ላይ ያላትን ተሞክሮ ለማስፋት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚያበረክቱት አስተዋፅኦ ትልቅ ሊሆን እንደሚገባ ተገልጿል፡፡

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ የሳተላይት መቆጣጠሪያ ጣቢያውን ለማስንባት ከ100ሺህ ዶላር በላይ ማውጣቱን እና ከሳተላይት የሚመጡ መረጃዎችን መሰብሰብና ሳተላይቱ ምን አይነት መረጃዎችን መሰብሰብ እንደሚገባው ትእዛዝ የሚተላለፍበት ነው ተብሏል::

ማዕከሉ ኢትዮጵያ በ2012 ዓ.ም ወደ ህዋ ትልካለች ተብሎ ለሚጠበቀው ሳተላይት በእውቀት ወይም በምርምር መደገፍ ይችላል ተብሎ ይጠበቃል::

የኮሪያ መንግስት ለዚህ የስፔስ ቴክኖሎጂ ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቋል::

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami