በማዳስካር ሁለተኛው ዙር የምርጫ ቅስቀሳ ተጀምሯል
አርትስ 27/03/2011
በመጀመሪያው ዙር ምርጫ ከተቀናቃኛቸው ከአራት በመቶ ባነሰ ድምፅ ተበልጠው ሁለተኛ ተመራጭ የሆኑት ማርክ ራቫሎ ማናና ቀጣዩ ድል የሳቸው እንደሆነ በኩራት እየተናገሩ ነው፡፡
ራቫሎማናና የመጨረሻ ፍልሚያቸውን የሚያደርጉት እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2014 በሀይል ከስልጣናቸው ካስወገዷቸው ከአንድሪ ራጆሊና ጋር ነው፡፡
ሁለቱ የቀድሞ የማዳጋስካር ፕሬዝዳንቶች ከዚያን ወቅት ጀምሮ የጎሪጥ ነው የሚተያዩት፡፡ አሁን ዳግም ወደ ስልጣን ለመምጣት የሚያደርጉት ፉክክር ደግሞ ይበልጥ አንዱ በሌላው ላይ ጣቱን እንዲቀስር በር ከፍቷል ፡፡
በኔና በሱ መካከል ያለውን ልዩነት ተመልከቱ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡ እናም በመጨረሻው ቀን ያን ክፍተት በመሙላት ድሉን ለመጎናፀፍ የሚያግደኝ የለም ብለዋል ለሮይተርስ ሲናገሩ፡፡
ባለፈው ወር በተደረገው ምርጫ ያልተሳተፉ ወደ 10 ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎች በአሁኑ ምርጫ በነቂስ ወጥተው ድምፃቸውን እንዲሰጡም ራቫሎማናና ጥሪ አቀርበዋል፡፡
በመጀመሪያው ዙር ምርጫ በቂ ድምፅ ሳያገኙ ቀርተው ከውድድሩ ውጭ የሆኑት 34 እጩወችም ድጋፋቸውን እንደሚሰጧቸው ከወዲሁ ተስፋ አድርገዋል፡፡
የወቅቱ ፕሬዝዳንት ራጃወ ናሪማም ፒያኒና በአንደኛው ዙር ውድድር የደረሰባቸውን ሽንፈት ተቀብለው ይህ ለማዳስካራዊያን ዲሞክራሲቃዊ ድል በመሆኑ ታላቅ ቀን ነው በማለት ሂደቱን አሞካሽተውታል፡፡
የማዳስካር ሁለተኛ ዙር ምርጫ በፈረንረጆቹ ታህሳስ 19 እንደካሄድ የሀገሪቱ ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት መወሰኑ ይታወሳል፡፡