Ethiopia

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የአመቱ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴቶች ዝርዝር ውስጥ ተካተቱ

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የአመቱ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴቶች ዝርዝር ውስጥ ተካተቱ

አርትስ 28/03/2011

ፕሬዝዳንቷን የአውሮፓውያኑ  2018 ዓመተ ምህረት የአለማችን 100  ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴቶች ዝርዝር ውስጥ ያካተተው ፎርብስ መፅሄት ነው፡፡

መፅሔቱ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ ብቸኛዋ ሴት ርዕሰ ብሄር መሆናቸውን አንስቶ በቅርቡ ሲመረጡ ለሀገራቸው ፓርላማ የሴቶች ድምፅ ሆነው እንደሚሰሩ እና ለሰላም ትኩረት እንደሚሰጡ መናገራቸውን ጠቅሷል።

ፎርብስ ለዓመታት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ያገለገሉትን ለረጅም ጊዜ በዲፕሎማትነት ያገለገሉት ሳህለወርቅ ዘውዴ ፕሬዚዳንት ሆነው መመረጣቸው በኢትዮጵያ ለፆታ እኩልነት መስፈን ተምሳሌታዊ ነው ሲል አስነብቧል፡፡

ፕሬዚዳንቷ በዘንድሮው የፎርብስ መፅሄት ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ ብቸኛ አፍሪካዊት ሴት ናቸው፡፡

ዝርዝሩ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ  የጀርመኗ መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል፣ የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬዛ ሜይ፣ የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም አይ ኤም ኤፍ ሀላፊ ክርስቲን ላጋርድ፣ ኦፕራ ዊንፍሬይን ጨምሮ ፖለቲከኛ፣ የንግድ ሰው፣ ምሁራን እና ስፖርተኞችን አካትቷል፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami