EthiopiaPolitics

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ እና በጣሊያን መካከል ያለው የፖለቲካ ግንኙነት በኢኮኖሚ ትብብር ሊደገፍ ይገባል አሉ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ እና በጣሊያን መካከል ያለው የፖለቲካ ግንኙነት በኢኮኖሚ ትብብር ሊደገፍ ይገባል አሉ

አርትስ 28/03/2011

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ከጣሊያን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢማኑኤላ ዲላሪ  ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ዶክተር ወርቅነህ በኢትዮጵያ እና በጣሊያን መካከል ያለው የፖለቲካ ግንኙነት በኢኮኖሚ ትብብር መደገፍ አለበት ብለዋል።

የጣሊያን ባለሀብቶች ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲሰማሩ እና ጣሊያን በሃገሪቱ የሚካሄደውን የመሰረተ ልማት ግንባታም እንድትደግፍ  ጥሪ አቅርበዋል።

በአፍሪካ ቀንድ የሰላምና መረጋጋት ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራትም ኢትዮጵያ ዝግጁ መሆኗን ነው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ  የተናገሩት።

መረጃው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ነው።

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami