ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከ140 የስድስተኛ ክፍል ተማሪዎች ጋር ተነጋገሩ
አርትስ28/03/2011
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ከመጡ ተማሪዎቹጋር የተነጋገሩት 13ኛውን የብሔር ብሔረሰቦች ቀንን በማስመልከት ነዉ፡፡
በጠ/ሚኒስተር ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ዉስጥ ዶክተር አብይ ከተማሪዎቹ ጋር በነበራቸው ቆይታ ከመገለልና ልዩነትን ከማቀንቀን ይልቅ ሰፋ ያለ አመለካከትን፤ የእርቅን፤
የአንድነትን፤ እና የትብብርን አስፈላጊነት አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
ጠ/ሚኒስትሩ ለተማሪዎች ሲናገሩ ሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች የራሳቸው ጥበብ፤ ቋንቋ፤ ማንነት፤ እና አገር በቀል ዕውቀት ባለቤት መሆናቸውን ከግምት ማስገባት ታላቅ ትምህርት እና ግንዛቤ ለመውሰድ እድል እንደሚሰጥ በማሰብ ሰብአዊነትን እንዲሹ
መክረዋል።