EthiopiaHealth

በኢትዮጵያ በየዓመቱ ህይወታቸውን ከሚያጡት ሰዎች መካከል ከ50 በመቶ በላይ የሚሆኑት ተላላፊ ባልሆኑ ህመሞች ምክንያት ነው ተባለ

በኢትዮጵያ በየዓመቱ ህይወታቸውን ከሚያጡት ሰዎች መካከል ከ50 በመቶ በላይ የሚሆኑት ተላላፊ ባልሆኑ ህመሞች ምክንያት ነው ተባለ

አርትስ 30/03/2011

 

 ከነዚህም መካከል ካንሰር፣ የስኳር ህመም እና ከመተንፈሻ አካላት ጋር የተያያዙ ህመሞች ከፍተኛውን ቁጥር ይይዛሉ፡፡

በአሁኑ ሰዓት 2 ነጥብ 6 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን የስኳር ህመም ያለባቸው ሲሆን 16 በመቶ ያህል አዋቂዎች የደም ግፊት ህመም እንዳለባቸው ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ ከከተሞች መስፋፋት ጋር ተያይዞ የአመጋገብ እና የአኗኗር ዘይቤ መቀየር ለችግሩ መስፋፋት ጉልህ ድርሻ አበርክቷል፡፡ ጤናማ ያልሆነ አመጋገብና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አለማድረግ ዋነኛ ተጠቃሾች ናቸው፡፡

ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመከላከል በየወሩ የተመረጡ መንገዶችን ከተሸከርካሪ ፍሰት ነጻ በማድረግ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን የማድረግ መርሃ ግብር ጀምሯል፡፡

 በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የሚያገለግሉት ዶክተር ምትኩአዘውትሮ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ አብዛኞቹን ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን መከላከል ይቻላል ብለዋል፡፡  

አርትስ ያነጋገራቸው አስተያየት ሰጪዎችም እንዲህ አይነት እንቅስቃሴ መጀመሩ መልካም መሆኑን ተናግረው ቀጣይነት እንዲኖረው ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡  

በየወሩ ከሚካሄደው መርሃ ግብር ጎን ለጎን የጡት ካንሰር፣ የስኳር እና የደም ግፊት ነጻ የምርመራ አገልግሎት  ይሰጣል፡፡ ይህም ህመሙ ሳይባባስ አስፈላጊውን  ህክምናና ጥንቃቄ  ለማድረግ ይረዳል ነው ያሉት  ዶክተር ምትኩ፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami