Sport

እንግሊዛዊው ጆ ጎሜዝ ከሊቨርፑል ጋር እስከ 2024 ለመቆየት ተስማምቷል

እንግሊዛዊው ጆ ጎሜዝ ከሊቨርፑል ጋር እስከ 2024 ለመቆየት ተስማምቷል

አርትስ ስፖርት 01/04/2011

ዘንድሮ በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ እንደ ሊቨርፑል የተከላካይ መስመር ተመስጋኝ የለም ቢባል ማጋነን አይሆንም፤ ለጥንካሬው ምክንያት ከሆኑት ተጨዋቾች መካከል ደግሞ የ21 ዓመቱ እንግዛዊው ጆ ጎሜዝ ተጠቃሽ ነው፤ ይህ ተጫዋች በ2015 ነበር ከቻርልተን አትሌቲክ ቀያዮቹን የተቀላቀለው፡፡ በየርገን ክሎፕ ቡድን ውስጥ ቅድሚያ ተመራጭ ከሚሆኑት አንዱ የሆነው ጎሜዝ እስከ 2024 በመርሲ ሳይዱ ክለብ ቀዩን ማሊያ እያጠለቀ ግልጋሎቱን ለመቀጠል ተስማምቷል፡፡

ጆ ጎሜዝ ‹‹ክለቡን እወዳለሁ፤ እዚህ መጫወትና መማርን እወዳለሁ እናም በዚሁ ለመቀጠል በመስማማቴ ደስተኛ ነኝ›› ብሏል፡፡

ተጫዋቹ እምነት የተጣለበት በክሎፕ ብቻም ሳይሆን በእንግዝ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት ጭምር ነው፤ ባለው አቅምም ሶስቱን አናብስት እያገለገለ ይገኛል፡፡

ጎሜዝ አክሎም ‹‹ብዙ የተለያዩ ዝቅታዎችና ከፍታዎች ነበሩ›› ያለ ሲሆን ‹‹አሁን አራተኛ የውድድር ዓመት ላይ ብገኝም እያንዳንዱ የውድድር ዓመት የተለያዩ ናቸው፤ በግልፅ በመንገዴ ውስጥ ጥቂት የኋሊት ጉዞ ያሳለፍኩ ቢሆንም የጉዞዬ አንድ አካል ናቸውና የምወዳቸውና የምቀበላቸው ናቸው፤ ብዙም ተምሬባቸዋለሁ›› ሲል ገልጧል፡፡

 

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami