በጋምቤላና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ውስጥ በሚገኙ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎች ትምህርት ቤቶች ሊገነቡ እንደሆነ ዩኒሴፍ አስታወቀ
አርትስ 02/04/2011
ዩኒሴፍ ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ የትምህርት ቤቶቹ ግንባታ የሚከናወነው ”ትምህርት ቆሞ አይጠብቅም” በሚል ለትምህርት በተያዘው 15 ሚሊዮን ዶላር በጀት ነው።
በፕሮጀክቱ በሰብዓዊ ቀውስ ውስጥ የሚገኙ ታዳጊዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ እንደሚሆን ይጠበቃል።
ሶስት ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ፣ ባለ 41 ክፍሎች ስምንት ሁለተኛ ደረጃ እና ባለ 84 ክፍሎች አራት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግንባታ የሚከናወን መሆኑን መግለጫው አትቷል።