AfricaPolitics

ራማፎሳ የካቢኔ አባሎቻቸውን ሀገራችሁን አስቀድሙ እያሉ ነው

ራማፎሳ የካቢኔ አባሎቻቸውን ሀገራችሁን አስቀድሙ እያሉ ነው

አርትስ 02/04/2011

ጃኮቭ ዙማን ተክተው ወደ ስልጣን የመጡት የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲርል ራማፎሳ የሀገራቸውን ኢኮኖሚ ካገባበት ችግር ለማውጣት ደጋግመው ቃል ሲገቡ ይደመጣሉ፡፡

ፕሬዝዳንቱ አሁን በደቡብ አፍሪካ ያለው የኢኮኖሚ አለመረጋጋት እንዳይባባስ በማሰብ ለህዝብ ተወካዮች አባላት ሊደረግ የታሰበውን  የደሞዝ ጭማሬ ውድቅ አድርገውታዋል፡፡

አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው ከፕሬዝዳንቱ ውሳኔ ቀደም ብሎ የመንግስት ኮሚሽን ለሁሉም የመንግስት ሰራተኞች የ4 በመቶ ደሞዝ ጭማሬ እንዲደረግላቸው ሀሳብ አቅርቦ ነበር፡፡

ሆኖም ፕሬዝዳንት ራማፎሳ ከግለሰቦች ጥቅም የሀገር ጉዳይ ስለሚቀድም የደሞዝ ጭማሬው የማይታሰብ ነው ብለዋል፡፡

ውሳኔው የኮሚሽኑን ሀሳብ ለማጣጣል ታስቦ ሳይሆን ሀገሪቱ ያለችበትን ችግር በማገናዘብ የተላለፈ ነው ብሏል ከፕሬዝዳንቱ ፅህፈት ቤት የወጣው መግለጫ፡፡

ፕሬዝዳንት ራማፎሳ ከ9 ወራት በፊት የቀድሞውን የጃኮቭ ዙማን የካቢኔ አባላት ቀይረው አብዛኛቹን በአዲስ መተካታቸው ይታወሳል፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami