Ethiopia

የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ፅህፈት ቤት እንደ አዲስ ሊደራጅ ነው ተባለ

የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ፅህፈት ቤት እንደ አዲስ ሊደራጅ ነው ተባለ

አርትስ 03/04/11

 የምክር ቤቱ ፅህፈት ቤት ሶስት ምክትል ፀሐፊዎች እንዲኖሩት የሚያስችል የማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡

ለፅህፈት ቤቱ የሚመደበው ዳይሬክተር እንደ ቀድሞው በሹመት ሳይሆን በውድድር ላይ ተመስርቶ ይቀጠራል ይላል ረቂቁ፡፡

እንደ አዲስ የሚደራጀው የምክር ቤቱ ፅህፈት ቤት መረጃዎችን ለሕዝብ የሚያደርስበት የብድሮድካስት ስርጭት ስልጣን እንዲኖረው በህግ ማሻሻያው ተካቷል፡፡

በተጨማሪም ጥናትና ምርምር እንዲያደርግ የሚፈቀድለት ይሆናል፡፡
ምክር ቤቱ በእውቀትና በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔም እንዲሰጥ ብቃት ያለው አማካሪ ጽህፈት ቤቱ ይኖረዋል ተብሏል፡፡

ረቂቅ አዋጁ ከመፅደቁ በፊት ለዝርዝር እይታ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ተመርቷል ሲል ሸገር ዘግቧል፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami