EthiopiaHealthRegions

ጊኒ ዎርምን ከኢትዮጵያ ለማጥፋት የአመራር አካላት ቁርጠኝነት ይፈለጋል ተባለ

ጊኒ ዎርምን ከኢትዮጵያ ለማጥፋት የአመራር አካላት ቁርጠኝነት ይፈለጋል ተባለ

አርትስ 03/04/11

ይህንን ያሉት የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶክተር አሚር አማን ናቸው።

የጊኒ ዎርም በሽታን ለማጥፋት እየተከናወኑ ያሉትን ስራዎችን የሚገመግው 23ኛው ሀገር አቀፍ ዓመታዊ እቅድ የአፈፃፀም ግምገማ ትናንት በጋምቤላ ከተማ ተጀምሯል።

ሚኒስትሩ በዚሁ ግምገማ ላይ እንዳሉት ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት በጤናው ዘርፍ በርካታ ውጤቶች ቢመዘገቡም የጊኒ ዎርም በሽታን በማጥፋት ረገድ የተከናወኑት ስራዎች ዝቅተኛ ናቸው።

ጊኒ ዎርም ከኢትዮጵያና አራት ሃገራት በቀር በየትኛውም የዓለም ሃገር የሌለ በሽታ ነው ብለዋል።

በሽታው ከኢትዮጵያ ሊጠፋ ያልቻው በየደረጃው የሚገኙ የአመራር አካላት በቁርጠኝነት፣ ተቀናጅቶ ያለመስራትና የምርምርና ጥናት ስራዎች ችግሮች መሆናቸውን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

የጊኒ ወርም በሽታን በ2019 ከኢትዮጵያ  ለማጥፋት ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ።

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami