EducationEthiopia

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ እጋጠመ ያለዉን የሰላም እጦት ለመቅረፍ መንግስት እየሰራበት ነዉ አሉ

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ እጋጠመ ያለዉን የሰላም እጦት ለመቅረፍ መንግስት እየሰራበት ነዉ አሉ

አርትስ 04/04/2011

  በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለመማር ማስተማር ሂደቱ ሰላማዊ ሁኔታን ለመፍጠር የመማር ማስተማር ሂደትን በሚያውኩ ችግሮችና መፍትሄዎች ላይ ጥናት መካሄዱንም ተናግረዋል፡፡

በትናንትናው ዕለት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የመማር ማስተማር ችግርን ለመቅረፍ በተካሄደዉ  ዉይይት ላይ አቶ ደመቀ ሁሉም ባለድርሻ አካል ሀላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በከፍተኛ ትምህርት ተቋመት ለሚፈጠረው ችግር እንደ መንስኤ ከተጠቀሱት ጉዳዮች ውስጥም ለተቋማቱ  የሚመጥን አመራር አለመኖር ችግሮች ሲነሱም ለችግሮች አፋጣኝ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ የማባባስ አዝማሚያ ማሳየት፤ የራስን የፖለቲካ ፍላጎት በሌሎች ላይ የመጫን ፍላጎት ያላቸው መምህራንና አመራሮች መኖር፣ የመውጫ ፈተና ከተቋም ተቋም የተለያየ መሆን ፣የተማሪዎች ወጥ ያልሆነ የምደባ ስርዓት እና  ተፈላጊነታቸው ያልተረጋገጡ የትምህርት ክፍሎች መኖርና እንደሆነም ተጠቅሰዋል።

ከመፍትሄ ሃሳቦች ውስጥም በተቋማቱ ምንም አይነት የፖለቲካም ሆነ የሃይማኖት እንቅስቀሴ እንዳይኖር መከታተል፣ ለተማሪዎች አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችንና መሰረተ ልማቶችን በፍጥነት ማስተካከል ፣በዩኒቨርሲቲዎች ዙሪያ የሚገኙ የንግድ ቤቶችን ተግባር መፈተሽና ሁከት ፈጣሪ የሆኑ ተማሪዎችን መለየትና እርምጃ መውሰድ የሚሉ ሃሳቦች ተጠቁመዋል።

ዘገባዉ የፋና ነዉ፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami