Uncategorized

በቱርክ በባቡር አደጋ ምክንያት የዘጠኝ ሰዎች ህይወት አለፈ

በቱርክ በባቡር አደጋ ምክንያት የዘጠኝ ሰዎች ህይወት አለፈ

አርትስ 04/04/2011

አደጋው የደረሰው በእኛ ሰዓት አቆጣጠር ከማለዳው 2፡30 በቱርክ ዋና ከተማ አንካራ ውስጥ በሚገኝ የባቡር ጣቢያ ሲሆን አንድ በከፍተኛ ፍጥነት ላይ በነበረ ባቡር አማካኝነት ነው ተብሏል፤ በአደጋው ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ዘጠኝ ሰዎች ሲሞቱ ከ45 በላይ የሚሆኑቱ ደግሞ ጉዳት እንደገጠማቸው የአካባቢያዊ የመገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል፡፡

ከስፍራው የተገኙ ምስሎች እንሚያሳዩት የድንገተኛ አደጋ አገልግሎት ሰራተኞች፤ ሰዎችን ከአሰቃቂው ጉዳት ለመታደግ  እየሰሩ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

የአካባቢው ባለሥልጣናት ስለ አደጋው በከፍተኛ ፍጥነት ውስጥ የነበረ ባቡር ከሌላው ባቡር ጋር ተጋጭቶ ወደ ላይ እንደተስፈነጠረ አስታውቀዋል፡፡

አደጋው የተከሰተበት ስፍራ ከአንካራ ዋናው የባቡር ጣቢያ በ8 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በሚገኘው የማርሳንዲዝ ባቡር ጣቢያ ሲሆን ግጭት ፈጣሪው ባቡር ከአንካራ ወደ ምስራቅ ቱርክ ከተማዋ ኮንያ እያመራ እንደነበር ታውቋል፡፡

በበረዷማው የአየር ሁኔታ ሰፊ ቁጥር ያለው የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ከግጭቱ በኋላ በፍጥነት ደርሰው የሰዎችን ህይወት እየታደጉ እንደሚገኙ ተጠቁሟል፡፡ ጉዳተኞችም ወደ ሆስፒታል እየተወሰዱ ነው፡፡

የአካባቢው አስተዳዳሪ ቫሲፕ ሳሂን አደጋው እንዴት እንደተፈጠረ የቴክኒክ ምርመራዎች  እየተሰሩ እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡

ቢቢሲና አናዶሉ

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami