EthiopiaRegionsSport

ተቀማጭነታቸውን በአማራና ትግራይ ክልል ያደረጉት ክለቦች ከዚህ በኋላ የእርስ በእርስ ጨዋታውን በሜዳቸው ያደርጋሉ ተባለ

ተቀማጭነታቸውን በአማራና ትግራይ ክልል ያደረጉት ክለቦች ከዚህ በኋላ የእርስ በእርስ ጨዋታውን በሜዳቸው ያደርጋሉ ተባለ

አርትስ ስፖርት 05/04/2011

ከባለፈው ዓመት ህዳር ወር ጀምሮ ተቀማጭነታውን በሁለቱ ክልሎች ያደረጉ ክለቦች ከእግር ኳሳዊ ባለፈ ምክንያት የእርስ በእርስ ጨዋታቸውን በሜዳቸው አድርገው አያውቁም፡፡ ዘንድሮም ይህ ቀጥሎ ነበር፤ በቅርቡ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከእግር ኳስ ፌዴሬሽን እና ስፖርት ኮሚሽን ኃላፊዎች ጋር በመሆን የክልሎቹን አስተዳዳሪዎች ማወያየታቸው ይታወሳል፡፡

አሁን ደግሞ የትግራይ እና አማራ ክልል ክለቦች ትናንት ባደረጉት ስብሰባ የእርስ በእርስ ጨዋታዎቻቸውን በየሜዳቸው ለማድረግ ተስማምተዋል።

በጁፒተር ሆቴል በነበረው ስብሰባ የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶ/ር ሒሩት ካሳው፣ የስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ርስቱ ይርዳው፣ የሁለቱ ክልሎች ክለብ ተወካዮች፣ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አመራሮች እና ሌሎች የተገኙ ሲሆን ክለቦቹ የእርስ በእርስ ጨዋታዎቻቸውን በየሜዳቸው ለማድረግ ከስምምነት ላይ መድረሳቸው ተነግሯል።

ባለፉት አምስት ሳምንታት ሊደረጉ የነበሩና ወደ ሌላ ጊዜ ተሸጋግረው የነበሩት የባህር ዳር ከነማ እና ስሑል ሽረ፣ የፋሲል ከነማ እና መቐለ 70 እንደርታ እንዲሁም የመቐለ 70 እንደርታ እና ባህር ዳር ከነማ ጨዋታዎች በተያዘላቸው ሜዳዎች  ይደረጋሉ።

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami