ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለመጀመሪያ ጊዜ የሶማሊያን ምድር ረገጡ
አርትስ 05/04/2011
የፕሬዝዳንቱ ጉብኝት የኢትዮጵያ፣ የኤርትራና የሶማሊያ መሪወች ከአሁን ቀደም ያደረጉትን የሶስትዮሽ ስምምነት ተከትሎ የተደረገ ነው፡፡
ሶስቱ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት በመካከላቸው ለዓመታት የነበረውን አለመተማመን በማስወገድ ግንኙነታቸውን መደስ ከጀመሩ ወራት ተቆጥረዋል፡፡
የፕሬዝዳንት ኢሳያስ ታሪካዊ ጉብኝት በቀንዱ ሀገራት መካከል ያለው የእርስበርስ ግንኙነት በፍጥነት መለወጡን የሚያሳይ ነውተብሏል፡፡
ሲጂቲኤን እንደዘገበው ፕዝዳንት ኢሳያስ ከሶማሊያው አቻቸው ከሞሀመድ አብዱላሂ ፋርማጆ ጋር በፀጥታና በኢንቨስትመንት ዙሪያ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ውይይት ያደርጋሉ፡፡
ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ወደ ሞቃዲሾ ያቀኑት ፕሬዝዳንት ፋርማጆን የፓርላማ አባሎቻቸው ከኤርትራና ከኢትዮጵያ ጋር የሀገራችንን ጥቅም የማያስጠብቅ ስምምነት አድርገዋል ብለው በከሰሱበት ወቅት ነው፡፡
በዚህም ምክንያት በሞቃዲሾ ያለው የፀጥታ ሁኔታ ከወትሮው በተለየ እንዲጠነክር አተደርጓል ተብሏል፡፡
ኢትዮጵያና ኤርትራ ያደረጉት እርቀ ሰላም በአፍሪካ ቀንድ ሀገራት መካከል መነቃቃት መፍጠሩን ተከትሎ አስመራና ሞቃዲሾ የዲፕሎማሲ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር እየተጉ ይገኛሉ፡፡