አርትስ 08/04/2011
ድረገጹ የዉጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት በማስተዋወቅና በማስፋፋት የሃገሪቱን ምጣኔ ኃብታዊ እድገት ወደላቀ ደረጃ ለማሻጋገር ይረዳልም ተብሏል፡፡
ኮሚሽኑ ለአርትስ በላከዉ መግለጫ እንዳስታወቀዉ Web-based Investment Guide to Ethiopia/ከUnited Nations Economic Commission for Africa (ECA) እና ከUnited Nations Conference on Trade and Development (UNCTAD) ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነዉ፡፡
ድረ ገጹም የሃገሪቱን የኢንቨስትመንት አማራጮች ማስተዋወቅና የዉጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፍሰትን ለማሳደግ ያግዛል ተብሎ ይጠበቃል ፡፡
ድረገጹ የፊታችን ረዕቡ በኢሲኤ አዳራሽ በይፋ ተመርቆ ወደስራ ይገባል፡፡