Ethiopia

image correction to ኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ድንበር ዘለል የፋይናንስ ወንጀሎችን ለመከላከል ተሰማሙ

image correction to ኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ድንበር ዘለል የፋይናንስ ወንጀሎችን ለመከላከል ተሰማሙ

አርትስ 09/04/11

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  ሼክ አብዱላሂ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር በአቡዳቢ ተወያይተዋል::

ውይይታቸውም የሁለቱ አገሮች ግንኙነት የደረሰበትን አጥጋቢ ደረጃ አንስተው የተነጋገሩ ሲሆን፥ ይህንኑ ወዳጅነት የበለጠ በማጠናከር አገሮችን ተጠቃሚ ለማድረግ ተስማምተዋል፡፡

በአገር ውስጥ የተጀመረውን የህግ የበላይነት የማረጋገጥ ጥረት ለመደገፍ ሁለቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በኢኮኖሚ ላይ የሚፈፀምን ድንበር ዘለል ወንጀሎችን በጋራ ለመከላከልና ሲፈፀሙም ተቀናጅቶ ለመመርመርበሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ ተነጋግረዋል፡፡

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ በተሳተፉበት በዚህ ውይይት በኢንቨስትመንት፣ በግዥ እና ሌሎች ተዛማጅ ድንበር ዘለል ወንጀሎችን በጋራ ለመከላከል እና ለመዋጋት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ ከመግባባትደርሰዋል፡፡

በቀጣይ የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን መከላከል የሚካሄድ ጠንከራ ጥረትን በህግ መዕቀፍ ለማስደገፍ አብረው እንደሚሰሩም መነጋገራቸውን ነው የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያስታወቀው፡፡
ፋና እንደዘገበዉ ከውይይታቸውም በኋላ ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች በሀገሪቱ ያላቸውን ሁኔታ የሚያሻሽል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል።

 

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami