Ethiopia

የኢትዮጲያ አየር መንገድ ለ27 ዓመታት ተቋርጦ የቆየዉን የሞስኮ በረራ ጀመረ

የኢትዮጲያ አየር መንገድ ለ27 ዓመታት ተቋርጦ የቆየዉን የሞስኮ በረራ ጀመረ

አርትስ 09/04/11

በረራው በሳምንት 3 ቀን ከአዲስ አበባ ሞስኮ እንደሚደረግ ተነግሯል።

አየር መንገዱ ለአርትስ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው  ከ1983 አመተ ምህረት ጀምሮ ወደ ሞስኮ የሚያደርገውን በረራ አቋርጦ ነበር፡፡

የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም፥ አየር መንገዱ በሳምንት 3 ቀን ወደ ሞስኮ የሚጀምረው በረራው  አየር መንገዱ በአውሮፓ ያለውን  መዳረሻ ወደ 54 ያሳድገዋል ብለዋል።

ወደ ሞስኮ የተጀመረው በረራ ለንግድና ባህል ልውውጥ እንዲሁም ለቱሪዝምና ኢንቨስትመንት መስፋፋት ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታል ነው ያሉት።

በመርሃ ግብሩ ላይ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣ የሃይማኖት መሪዎችና የተለያዩ እንግዶች ታድመዋል።

የኢትዮጲያ አየር መንገድ ባለፈው ሳምንት ወደ ብሪታኒያ ማንቸስተር በረራ መጀመሩም የሚታወስ ነው፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami