የአማራ ክልልና የፌዴራል መንግስት ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በክልሉ ለሚገኙ ዜጎች የ36 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረጉ
አርትስ 10/04 /2011
የክልሉ መንግስት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አሰማህኝ አስረስ፥ ከተለያዩ አካባቢዎች ለተፈናቀሉ ዜጎች የክልሉ መንግስት የ28 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉን የገለፁ ሲሆን፥ የፌዴራል መንግስት ደግሞ የ8 ሚሊየን ብርና የ7 ሺህ ኩንታል እህል ማድረጉን ተናግረዋል።
ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የተፈናቃዮችን ፍላጎት መሰረት ተደርጎ ክልሉ ከፌዴራል መንግስት ጋር በመሆን ወደ ነበሩበት የመመለስ ስራ እንደሚሰራ አቶ አሰማህኝ አስታውቀዋል።
ከዚህ ባለፈ ከክልሉ ውጭ ለሚኖሩ የክልሉ ተወላጆች ደህንነትና ሰላም በክልሉ መንግስት የተዋቀረ ግብረ ሀይል መቋቋሙን ሀላፊ ጠቁመዋል ሲል ኤፍቢሲ ዘግቧል።