Africa

የታንዛኒያ ተቃዋሚ ፓሪቲዎች ሀገሪቱ የኋልዮሽ ጉዞ ላይ ናት አሉ

አርትስ 10/04/2011

ተቃዋሚ ፓርቲዎቹ የጆን ማጉፉሊን አስተዳደር ለመሞገት ሲሉ ቅንጅት የፈጠሩ ሲሆን ታንዛኒያ በአሁኑ ወቅት  የዴሞክራሲ እጦት ላይ መሆኗን ተናግረዋል፡፡

አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው ፓርቲወቹ ሀገራችን በአምባገነን አገዛዝ ስር እንደወደቀች ሁሉም ዜጋ ሊገነዘብ ይገባል የሚል ጠንከር ያለ መግለጫ ነው የሰጡት፡፡

በ2019 ዴሞክራሲን ለማረጋገጥ እና ህገ መንግስታዊ ከለላወቻችን ተግባራዊ እንዲሆኑ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ህዝባዊ ንቅናቄ እናደገርጋለንም ብለዋል፡፡

ተቃዋሚ ፓርቲዎችን የሚያዳክም የህግ ማሻሸያወች መደረጋቸው ሀገሪቱ ምን ያህል የደሞክራሲ  ቸደግር እንዳለባት  በግልፅ የሚያሳይ ነው ሲሉም የማጉፉሊን መንግስት ወቅሰዋል፡፡

የፓቲወቹ ጥምረት መንግስትነ ጥያቂያችንን የማይሰማ እና ህገ መንግሰታዊ መብቶቻችንን የሚጋፋ ከሆነ ፍርድ ቤት እደናቆመዋለን በማለትም አስጠንቀቅዋል፡፡

የታንዛኒያን መንግስት ለመሞገትና ቅንጅት የፈጠሩት ፓርቲወቹ አስቸኳይ ለውጥ ያስፈልጋል የሚለውን መግለጫቸውን ስድስት የሚሆኑ ፓርቲወች ተስማምተው በፊርማቸው ድጋፋቸውን ሰጥዋል፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami