አርትስ ስፖርት 11/04/2011
በካራባዎ ዋንጫ ትናንት ምሽት የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች ተካሂደዋል፤ በሰሜን ለንደን ደርቢ አርሰናል በፍላይ ኢምሬትስ ከቶተንሃምተጫውተው እንግዳው ክለብ በሰን ሁንግ ሚን እና ደሊ አሊ ጎሎች 2 ለ 0 በመርታት ወደ ሩብ ፍፃሜው ተቀላቅሏል፡፡
በስታንፎርድ ብሪጅ ቼልሲ ከ በርንማውዝ ተጫውተው፤ ሰማያዊዎቹ በኢዲን ሃዛርድ ብቸኛ ግብ 1 ለ 0 በመርታት ወደ ሩብ ፍፃሜውተዋህዷል፡፡
ማክሰኞ ምሽት ማንችስተር ሲቲና ቡርቶን አልቢዮን ተጋጣሚዮቻቸውን በመርታት ወደ ግማሽ ፍፃሜው አልፈዋል፡፡
በግማሽ ፍፃሜ የዕጣ ድልድል ቶተንሃም ከ ቼልሲ በለንደን ደርቢ ሲገኛኑ፤ ማንችስተር ሲቲ ከ ቡርቶን አልቢዮን ይጫወታሉ፡፡
ዙሩ የደርሶ መልስ ግጥሚያ የሚኖረው ሲሆን የመጀመሪያ ጨዋታዎች ጥር 8 እና የመልስ ፍልሚያዎች ጥር 22/2019 ይደረጋሉ፤ ማንችስተርሲቲ እና ቶተንሃም በሜዳቸው የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ያከናውናሉ፡፡