EthiopiaPoliticsRegionsSocial

በቤኒሻንጉል ጉሙዝና የኦሮሚያ አጎራባች አካባቢዎችን የጸጥታ ችግር ለመፍታት የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት ስራ ጀመረ

አርትስ 12/04/2011

የአገር መከላከያ ሠራዊትና ፌዴራል ፖሊስ ከሁለቱ ክልሎች መንግስታት ጋር በመጣመር ያቋቋሙት ኮማንድ ፖስትበክልሎቹ አጎራባች አካባቢዎች የመሸገውን የታጠቀ ኃይል በመቆጣጠር የኅብረተሰቡን ደህንነት የማስጠበቅ ሃላፊነት አለበት።

መቀመጫውን በአሶሳ ከተማ  የሚያደርገው ኮማንድ ፖስት፣ ከሱዳን የጸጥታ ኃይሎች ጋር ተባብሮ እንደሚሰራም የኮማንድ ፖስቱ አባልና የቤኒሻንጉል ክልል  ፖሊስ ኮሚሽነር አቶ ሰይፈዲን ለኢዜአ ተናግረዋል።

የክልሎቹን ሕዝቦች እንቅስቃሴ ሲገድብና ጥናት ሲፈጽም የቆየው ይኸው የታጠቀ ሃይል በአቋራጭ ሥልጣን የመያዝ ፍላጎትያለው ነው ያሉት አቶ ሰይፈዲን ዋና ዓላማውም የተጀመረውን አገራዊ ለውጥ ማደናቀፍ ነው ብለዋል።

በተጨማሪም ይህ ኃይል ከየትኛውም ብሔርና የፖለቲካ ድርጅት ጋር ግንኙነት እንደሌለው ተደርሶበታል ነው ያሉት።

የብሔራዊ የጸጥታና የደህንነት ምክር ቤት ውሳኔን ተከትሎ የአገር መከላከያ ሠራዊት አካባቢውን መቆጣጠሩ የኃይሉንእንቅስቃሴ እንዳዳከመውም ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።

በ25 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው የካማሽና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች አዋሳኝ አካባቢ ከጸጥታ ኃይሎች በስተቀር የጦርመሣሪያ ይዞ መንቀሳቀስ የማይቻልበት ቀይ መስመር ተደርጎ በኮማንድ ፖስቱ ተለይቷል።

ኮማንድ ፖስቱ ሕገ-መንግሥቱን መሠረት በማድረግ ብቻ ያለምንም የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሥራውን ያከናውናል ነው ያሉት አቶ ሰይፈዲን።

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami