AfricaEconomyEthiopiaPolitics

ሃገራዊ የገቢ ንቅናቄ ተጀመረ

አርትስ ታህሳስ 12 2011

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግብርን በተመለከተ የተሳሳተ አመለካከት ያላቸው ሰዎች  ወደ ስርዓት እንዲገቡ አሳሰቡ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት “ግዴታየን እወጣለሁ፤ መብቴንም እጠይቃለሁ” በሚል መሪ ቃል የገቢዎች ሚኒስቴርባዘጋጀው ሃገራዊ የገቢ ንቅናቄ ዛሬ በይፋ በተጀመረበት ወቅት ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት ኢትዮጵያ እንድታድግና በሰላም እና በልማት ውስጥ እንድታልፍ ለማድረግ ስለግብር ያለንንደካማ አመለካከት ማሸነፍ አለብን ።

እንደጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ማሳሰቢያ ግብርን የሚያጭበረብሩ ዜጎችን እንደ ብልጥ መመልከት መቆም አለበት።

በአንጻሩ በአግባቡ ግብር የሚከፍሉትን ዜጎች መንግስትንና ልጆቹን እንደሚወድ ዜጋ እንመለከታቸዋለን ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያለንግድ ፍቃድ መነገድ፣ ሙስና፣ በግብር ማጭበርበር እና ሌሎች ህገወጥ የሆኑ አካሄዶች የዘርፉማነቆዎች መሆናቸውን አንስተው ይህ ሊቆም ይገባልም ነው ያሉት።

በመሰል ድርጊቶች የሚሳተፉ አካላትም ከዚህ ሰዓት ጀምሮ ከድርጊታቸው  እንዲታቀቡ እናሳስባለን ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ።

በአግባቡ የሚከፍሉ ግብር ከፋዮችን ለማበረታታት እየተሰራ ነው ያሉት ዶክተር አብይ ግብር ከፋዩ ሳይጉላላ ተንቀሳቃሽስልክን ጨምሮ ፈጣን የክፍያ ስርዓት እንደሚዘረጋም ተናግረዋል።

ንቅናቄውን ለማስጀመር በአፍሪካ ህብረት በተካሄደ መድረክ ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፥ ከግብር ጉዳይ ጋርበተያያዘ የተሳሳተ አመለካከት ያላቸው ሰዎች ቀኑ ከመጨለሙ በፊት ወደ ስርዓት እንዲገቡም አሳስበዋል።

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami