EducationEthiopia

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአምቦ መሰናዶ ትምህርት ቤት ድንገተኛ ጉብኝት አደረጉ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአምቦ መሰናዶ ትምህርት ቤት ድንገተኛ ጉብኝት አደረጉ

አርትስ 15/04/2011

የመጀመሪያውን ክፍለ ጊዜ እያስተማርን ያልጠበቅነው የፀጥታ ሀይል ግቢውን ወረረው

የሄሊኮፐተር ድምጽ ተሰማ ፤ባላሰብነዉ ሰዓት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትምህርትቤታችን ዉስጥ ተገኙ ደስታና ድንጋጤን በአንድ ላይ አስተናገድን፤ከትምህርት ቤቱ መምህራን  አንዱ  ለአርትስ ቲቪ እንደተናገሩት፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባደረጉት ድንገተኛ የትምህርት ቤቱ ጉብኝት ተማሪዎች መደሰታቸውንና እርሳቸው ያስተላለፉትን መልዕክት በጉጉትና በጥሞና ሲያደምጧቸው ነበር፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው በዚህ ትምህርት ቤት ቀደም ሲል ተምረው የነበሩ ሰዎች ከፍተኛ ደረጀ እንደደረሱና ትምህርት ቤቱ በመልካም ስም እያስጠሩ እንደሆነ ተናግረው፤ እናንተም ዛሬ ጠንክራችሁ ካልተማራቹ ለሀገራቹ ማድረግ የምትፈልጉትን ማድረግ አትችሉምና ቅድሚያ መስጠት ያለባችሁ ነገር ቅድሚያ ስጡ ፤ጠንክራቹ ተማሩ ብለዋቸዋል፡፡

እሳቸው ግቢውን ለቀው ከወጡ ከአንድ ሰዓት በኋለ ከአርትስ ጋር ቆይታ ያደረገችው ተማሪ ሴና አዳነ የደስታ ስሜቱ አብሯት ነበር፤ እሳቸውን ፊትለፊት እያዩ ምክርን መስማት ደስ ይላል ብላ የወደ ፊት ሃገር ተረካቢ ናችሁ ሲሉን እንደማደርገው በውስጤ እርገጠኛ ሆንኩ ብላናለች፡፡

በትላንትናው ዕለት  በከተማዋ ከዛሬ ሰኞ ጀምሮ የስራ ማቆም አድማና የተቃውሞ ሰልፍ መካሄድ አለበት የሚሉ በራሪ ወረቀቶች ነበሩ ያሉን ተማሪዋና መምህሩ ፤በምንም መልኩ ቦታ አልሰጠነውም ተማሪውም በትምህርት ገበታው ተገኝቷል፤ ሰራተኛውም ስራውን በአግባቡ እየሰራ ነዉ ብለዉናል፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami