EthiopiaRegions

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የክልሉን ሰላምና ደህንነት በሚያደፈርሱ አካላት ላይ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ ነኝ አለ

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የክልሉን ሰላምና ደህንነት በሚያደፈርሱ አካላት ላይ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ ነኝ አለ

አርትስ 15/04/2011

ህግን በመተላለፍ የክልሉን ሰላምና ደህንነት በሚያደፈርሱ አካላት ላይ እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል ጥብቅ ትዕዛዝ ለሁሉም ዞኖች መተላለፉን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታዉቋል።

በምዕራባዊ የክልሉ አካባቢዎች ያጋጠመውን የፀጥታ ችግር በውይይትና በትዕግስት ለመፍታት ሞክሬያለሁ ያለው ፖሊስ ኮሚሽኑ፤ እስከ ህይወት መስዋዕትነት የደረሰ ዋጋ አስከፍሎኛል ሲልም ገልጿል።

ኮሚሽነር አለማየሁ እጅጉ እንደገለፁት በቄለም ወለጋ የተገደሉትን 2 የዞን ፖሊስ አመራሮችን ጨምሮ የ12 ፖሊስ አባላት ህይወት ማለፉንና 77 ፖሊሶች መቁሰላቸውን ተናግረዋል።

በተጨማሪም  የሚሊሻ አባላትን ጨምሮ በ40 የፀጥታ አካላት ላይ የመቁሰል አደጋ፣ የ29 ነዋሪዎች ደግሞ ህይወታቸው ማለፉን ገልፀዋል።

በአካባቢው የሚደርሰው ጉዳት ከዚህም በላይ ነው ያሉ ሲሆን የግለሰቦችን ሳይጨምር ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ከባንክ መዘረፉን ገልፀዋል።

ታጣቂዎቹ በአካባቢው ካለ ፖሊስ ጣቢያ 2072 ክላሺንኮቭ ጦር መሳሪያም ዘርፈዋል ተብሏል፡፡

ትዕግስቱ ከአንድ ወገን መሆኑ ዋጋ እንዳስከፈለ እና ህግን የሚያውኩ አካላትን ለህግ የማቅረብ ስራው ተጠናክሮ ይቀጥሏል ተብሏል።

ለዚህም ለሁሉም ዞኖች ጥብቅ መመሪያ ተላልፏል እንደ ፖሊስ ኮሚሽነሩ ገለፃ፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami