የኦሮሚያ ፀረ ሙስና ኮሚሽን በክልሉ በሙስና የጠረጠራቸዉን 56 ሰዎችን በህግ ቁጥጥር ስር አዋለ
አርትስ 15/04/2011
ኮሚሽኑ በክልሉ የተለያዩ መስሪያቤቶች የሚገኙ በተለያየ ሙያና የስራ ሃላፊነት ላይ የሚገኙ የክልሉ ሰራተኞች ላይ ሲያደርግ የነበረውን ክትትል አጠናቆ ነዉ 56 ቱን በህግ ቁጥጥር ስር ያዋለዉ፡፡
ተጠርጣሪዎችን ተከታትሎ በቁጥጥር ስር የማዋሉ ስራ የሚቀጥል ሲሆን፤ ሰሞኑን እየተሰራ ባለው ስራና እየተወሰደ ባለው እርምጃ፤ የኮሚሽኑ ሃላፊዎች ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ እንደሚሰጡ የኦዲፒ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የገጠር ፖለቲካና የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ በፌስቡክ ገጻቸዉ ይፋ አድርገዋል፡፡