የ2018 አይረሴ የእግር ኳስ ትዝታዎች
አርትስ ስፖርት 16/04/2011
የፈረንጆቹ 2018 ዓመት ቢቢሲ በገፁ ባሰፈረው ዘገባ ዓመቱ በእግር ኳስ አስደናቂ እና አይረሴ ትዝታዎችን ትቶ እንዳለፈ ነው የተመለከተው፤ በተለያዩ ታላላቅ ውድድሮች የታጀበ ድንቅ ዓመትም ብሎታል ቢቢሲ፤ ወደ ትዝታዎቹ ልለፍ፡-
1፡ በዓለም ዋንጫ የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን የኮሎምቢያ አቻውን በመለያ ፍፁም ቅጣት ምት ያሸነፈበትና ግማሽ ፍፃሜውን የተቀላቀለበት መንገድ
2፡ ማንችስተር ሲቲ በፕሪምየር ሊጉ በጋብሪየል ጀሱስ ግብ 100ኛ ነጥቡን ያስመዘገበበት ጨዋታ
3፡ በዓለም ዋንጫው በኑዌር ስህተት ጀርመን ከዓለም ዋንጫው የተሰናተበተችበት ጨዋታ
4፡ ዩሊዬን ሎፔቴጉይ ከስፔን ብሔራዊ ቡድን መሰናት
5፡ የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ የታዩ ክስተቶች
6፡ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ሪያል ማድሪድ እያለ በቻምፒዮንስ ሊግ ዩቬንቱስ ላይ ያስቆጠራት የባይሳይክል ጎል
7፡ በማንችስተር ዩናይትድ የሞሪንሄ ስንብትና የሶልሻዬር ቅጥር
8፡ በዓለም ዋንጫው ያንፀባረቀው ምባፔ እንቅስቃሴ
9፡ የአርሰን ቪንገር ከአርሰናል መለየት
10፡ በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ሮማ የባርሴሎናን ሽንፈት የቀለበሰበት መንገድ፤ እንዲሁም
11፡ በኢራን እና ስፔን ብሔራዊ ቡድን በነበረ የዓለም ዋንጫ ጨዋታ የሚላድ ሞሀማዲ የእጅ ውርወራ ክስተት
ለእርስዎስ የትኛው ሁነት አይረሴ ሁኖ አለፈ?