EthiopiaPoliticsRegions

በኦሮሚያ የትጥቅ ትግል ላይ የነበሩ ሃይሎች ወደሰላማዊ ህይወት እየተመለሱ መሆኑ እየተነገረ ነው።

በኦሮሚያ የትጥቅ ትግል ላይ የነበሩ ሃይሎች ወደሰላማዊ ህይወት እየተመለሱ መሆኑ እየተነገረ ነው።

አርትስ 17/04/11

የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ እንዳስታወቀው በኦሮሚያ ክልል የትጥቅ ትግል ለማድረግ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ በርካታ ግለሰቦች ወደሰላማዊ ህይወት እየተመለሱ ነው።

እስካሁን ድረስ ብዛት ያላቸው ታጣቂዎች ለመንግስት እጃቸውን ሰጥተው ወደሰላማዊ ህይወት ተቀላቅለዋል ብሏል ፓርቲው።

የፓርቲው የገጠር ፖለቲካ አደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ እንደገለፁት ታጣቂዎቹ ወደሰላማዊ ህይወት እየተመለሱ ያለው የሀገር ሽማግሌዎች፣ አባ ገዳዎች እና የፀጥታ አካላት እያደረጉ ባለው ጥረት ነው።

በርከት ያሉ ታጣቂዎች ሰላማዊ ትግል ለማድረግና  በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ ያለውን ለውጥ ለመደገፍ ወስነው ወደ ሰላማዊ የትግል መስመር እየተመለሱ ይገኛሉ ብለዋል አቶ አዲሱ።

እንደአቶ አዲሱ መግለጫ ታጣቂዎች እያሳለፉ ያለውን ውሳኔ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ያበረታታል ።

ተመላሾቹ በፍላጎታቸው እና በችሎታቸው ወደስራ እንዲሰማሩ እንደሚደረግም ተናግረዋል።ዜናው የኢዜአ ነው።

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami