Ethiopia

ለውጡ እንዲቀጥል ለሰላም ትኩረት እንዲሰጥ ተጠየቀ

ለውጡ እንዲቀጥል ለሰላም ትኩረት እንዲሰጥ ተጠየቀ

አርትስ 17/04/11

በሀገሪቱ የተጀመረውን ለውጥ ለማስቀጠል የሰላም ጉዳይ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ተጠቆመ።

የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ህብረት እና የሀገር ሽማግሌዎች “ሠላም ለሁላችን በሁላችን” በሚል መሪ ቃል በሀዋሳ ከተማ ሀገር አቀፍ የሰላም ጉባኤ አካሂደዋል።

በጉባኤው ላይ የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ህብረት፣ የክልል የሃይማኖት ተቋማት ተወካዮች፣ የወጣት አደረጃጀቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳታፊዎች ነበሩ።

በኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ህብረት ጸሀፊ መጋቢ ዘሪሁን ደጉ በጉባዔው ላይ እንደተናገሩት፥ በኢትዮጵያ ለዘመናት በጋራ የዘለቀው ሰላም፣ አንድነትና አብሮነት ላይ በስፋት ለመስራት በሁሉም ክልሎች እንቅስቃሴዎች ተጀምረዋል።

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ በሁሉም አቅጣጫ ለውጥ ላይ ነች ያሉት የህብረቱ ጸሃፊ ይህንን ለውጥ የሚያደናቅፉ ጉዳዮችን በንቃት በመታገል ሁሉም አካል ለሰላም ዘብ ሊቆም ይገባል ብለዋል።

ለውጡን ማስቀጠል የሁላችንም ሀላፊነት በመሆኑ ሰላም፣ ልማትና ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል እንዲኖር ሁሉም ኢትዮጵያዊ መረባረብ አለበት ነው ያሉት።

እንደደቡብ ክልል ፕሬስ ሰክረተሪያት መረጃ ከሆነ በጉባኤው ተሳታፊ የነበሩ አስተያየት ሰጪዎች በስፋት ውይይት አድርገዋል።

በሀገሪቱም ሆነ በክልሉ ለተፈጠሩ ችግሮች መንስኤዎች ናቸው ያሏቸውን ሀሳቦች በማንሳት የመፍትሄ ሀሳቦችን አስቀምጠዋል።

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami