EthiopiaPoliticsSocial

አርበኞች ግንቦት ሰባት ፓርቲ አመፅና ትጥቅን መሰረት ያደረገ ትግል ኢትዮጵያን ወደ ውድመት ይመራታል አለ

አርትስ 17/04/11

 

የአርበኞች ግንቦት ሰባት ፓርቲ ዋና ጸሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት አመጽና ትጥቅን መሰረት ያደረገ ትግል ሃገሪቱን ወደውድመት ከመምራት በስተቀር ሌላ ጥቅም የለውም።

አቶ አንዳርጋቸው እንዳሉት ትግል ከአመፅ ነፃ በሆነ ሰላማዊ መንገድ ብቻ ሊካሄድ ይገባል።

አመፅ እና ትጥቅን መስረት ያደረገ ትግል ኢትዮጵያን ወደ ውድመት ከመምራት በስተቀር ሌላ ጥቅም እንደማይኖረው የተረዳው ግንባሩ፥ አባላቱበየትኛውም የአመፅ ድርጊት እንዳይሳተፉ ጥብቅ ማሳስቢያ ማስተላለፉንም አቶ አንዳርጋቸው ተናግረዋል።

ከግንቦት 7 አብዛኛዎቹ ታጣቂዎቹ ትጥቅ መፍታታቸውን የተናገሩት አቶ አንዳርጋቸው፥ ታጣቂዎቹ ወደ ካምፕ እንዲገቡ መደረጉንም ነው ያስታወቁት። ዘገበው የፋና ነው

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami