EthiopiaPoliticsRegionsSocial

የሀይማኖት አባቶች ከኦነግ አመራሮች ጋር ተወያዩ

የሀይማኖት አባቶች ከኦነግ አመራሮች ጋር ተወያዩ

አርትስ ታህሳስ 19 2011

በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶች እየተበራከቱ ዜጎችን ለሞት እና ለመፈናቀል እየዳረጉ መሆኑን ተከትሎ ለዚህ መፍትሄ መስጠት የውይይቱ ዋና አላማ ነው ተብሏል፡፡

በውይይቱም አቶ ዳውድ ኢብሳን ጨምሮ ከተለያዩ ሃይማኖቶች የተወጣጡ የሀይማኖት መሪዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች ተሳታፊ ነበሩ፡፡

የኢትዮጲያ ሀይማኖት ተቋማት ዋና ፀሃፊ መጋቢ ዘሪሁን ደጉ እንደተናገሩት የኦነግ አመራሮች እና አባላቶቹ ከወራት በፊት ወደሀገር ውስጥ ሲገቡ የክልሉ ህዝብ እና ኢትዮጲያዊያን በደስታ ነበር የተቀበሏቸው፣ ሆኖም ግን ብዙም ሳይቆይ በክልሉ አለመረጋጋት እና የሰላም እጦት ተከስቶ ዜጎች እየተጎዱ በመሆኑ ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡

በቀጣይም ከሌሎች ጉዳዩ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከሚመለከታቸው አካላት እና የሀገር ሽማግሌዎች ጋር ውይይት እንደሚደረግ ተነግሯል፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami