በኢትዮጵያ ከሚገኙ የጤና ተቋማት ውስጥ 62 በመቶ የሚሆኑን በዳታ ቤዝ የማስተሳሰር ስራ ተጠናቀቀ
አርትስ ታህሳስ 19 2011
እንደ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ገለጻ የጤና ተቋማቱ ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ስርዓትን እንዲከተሉ እና በመረጃዎች እንዲተሳሰሩ የማድረግ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል።
ሚኒስትሩ ዶክተር አሚር አማን መረጃን ከማዘመን ጋር ተያይዞ ዲጂታላይዝ እንዲሆኑ ወይም ዘመናዊ አያያዝ እንዲኖራቸው ማድረግ ፣ የመረጃን አጠቃቀም ማሳደግ እና የተቋማቱን አመራር የማስተካከል ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል።
ይህ አሰራር የዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ስርዓት ተግባራዊነትን ውጤታማ የሚያደርግ በመሆኑ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራበት ነው ብለዋል፡፡
ሚኒስትሩ ዶክተር አሚር አማን እንዳሉት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በተደረሰ ስምምነት ጤና ተቋማቱ በኢንተርኔት የማስተሳሰር እና ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ስርዓት ተግባራዊ እየተደረገ ነው።
ይህም ከካርድ ጀምሮ ሌሎች የህክምና አገልግሎቶች ዲጂታል እንዲሆኑ ከዚህ ቀደም ይሰራበት የነበረውን ማኑዋል በማስቀረት ተግባር አንዱ የህክምና ክፍል ውስጥ ያለ መረጃ ሌሎቹም የተቋሙ ክፍሎች ውስጥ በተመሳሳይ ጊዜ እንዲደርሱ ማድረግ ተችሏል።
ይህ ተግባራዊ እንዲሆን ከተደረገባቸው ጤና ተቋማት ውስጥ የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አንዱ ነው።
በሆስፒታሉ ከዚህ ቀደም የህክምና ካርድ ከማውጣት ጀምሮ ሌሎች የህከምና አገልግሎቶቹን ለማግኘት መረጃ የሚያዘው በወረቀት ላይ ነበር። ይህ አሰራር ተግባራዊ ከተደረገ በኋላ ግን የታካሚው መረጃ ዘመናዊ ሆኗል ፋና እንደዘገበው።