Uncategorized

የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በሶሪያ ዘግታው የነበረ ኤምባሲዋን ድጋሚ ከፍታለች

የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በሶሪያ ዘግታው የነበረ ኤምባሲዋን ድጋሚ ከፍታለች

አርትስ ታህሳስ 19 2011

የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በሶርያ መዲና ደማስቆ የሚገኘውንና ተዘግቶ የቆየውን ኤምባሲዋን ትናንት በድጋሚ መክፈቷን የሶርያ የኢንፎርሜሽን ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በ2011 በሶርያ የተቀሰቀሰውን ግጭት ተከትሎ በሶሪያ የነበረ ኤምባሲዋን መዝጋቷ ይታወሳል፡፡

አቡዳቢ የፕሬዚዳንት በሽር አል – አሳድ መንግስትን ለመገርሰስ በሚደረገው ትግል ውስጥ ለበርካታ ታጣቂዎች የረዥም ጊዜ ድጋፍ ሰጪ ሀገር ነበረች ተብላ ትታማም ነበር።

አሁን ግን የሶርያ መንግስት በታጣቂዎች ላይ የበላይነት ወስዷል፤ በታጣቂው ኃይል ተቆጣጥሯቸው የነበሩ ቦታዎችን ሁሉንም በሚባል ደረጃ በእጃቸው ውስጥ ማስገባታቸውን ተከትሎ የግጭቱ ንፋስ ተቀይሯል፡፡

የቀድሞ የደማስቆ ባላጋራ አቡ ዳቢም ኢምባሲዋን መክፈቷ፤ ከንፋሱ ጋር ስሌቷን መቀየሯን የሚያመላክት ነው ሲል ፕሬስ ቴለቭዥን ዘግቧል፡፡

የዚህ ሁሉ ሀሳብ መቀያየር የመጣው አሜሪካ በሶርያ ያለውን ሁሉንም ሀይሏን እንደምታስወጣ ማስታወቋን ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami