EthiopiaPoliticsSocial

የገቢዎች ሚኒስቴር የኦዲት ግኝት እርምት ለማድረግ እየሰራሁ ነዉ አለ

የገቢዎች ሚኒስቴር በፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የተሰጡ የኦዲት ግኝት አስተያየቶችን የእርምት እርምጃ ለመውሰድ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የውስጥ ኦዲት ዳይሬክተር አቶ ደሳለኝ ገመቹ ተናግረዋል፡፡

አቶ ደሳለኝ ገመቹ እንዳሉት፤ የገቢዎች ሚኒስቴር ከ2004 እስከ 2009 ዓ.ም. በዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ከተገኘበት 11.3 ቢሊዮን ብር የኦዲት ግኝት 1.2 ቢሊዮን ብር ተሰብስቧል፡፡

በተለያዩ ምክንያቶች በወቅቱ እርምጃ ያልተወሰደባቸውን ቀሪ የኦዲት ግኝቶች የእርምት እርምጃ እንዲወሰድባቸው በዋና መስሪያ ቤትና በ17 ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች ግኝቱ የሚመለከታቸውን የሥራ ክፍሎችን በማካተት የቴክንክ ኮሚቴ በሥሩ ያለው ዐብይ ኮሚቴተዋቅሯል፡፡

ኮሚቴዎቹ ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርጉና የውስጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬትም ሪፖርት በማጠናከርና በመመዝገብ ለሚመለከተው አካል እንደሚያቀርብ ገልጸዋል፡፡ ይህ መደረጉ ለዓመታት እየተንከባለለ የመጣውን የኦዲት ግኝት ለማስተካከል እንደሚያግዝ ዳይሬክተሩገልጸዋል፡፡

አርትስ 22/04/2011

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami