EthiopiaSportSports

የኢትዮጵያ ክለቦች የሊግ ውድድሮችን የሚመራ የሊግ አስተዳደር ጥር 7 ያቋቁማሉ ተብሎ ይጠበቃል

ክለቦች ራሳቸው ባቋቋሙት የሊግ አስተዳደር መመራት አለባቸው ተብሎ ባለፉት ዓመታት በተደጋጋሚ ቢነገርም ውጤታማ መሆን አልቻለም ።

ሶከር ኢትዮጵያ ድር ገፅ እንደዘገበችው አዲስ የመጣው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አመራሮች ክለቦች የራሳቸውን ውድድሮች ራሳቸው መምራት አለባቸው በማለት አደረጃጀቱን እንዲያስፈፅሙ አቶ ሰላሙ በቀለ፤ አቶ አስጨናቂ ለማ እና አቶ ሸረፋ ዴሌቾ መመረጣቸው ይታወሳል።

የሊግ ኮሚቴ ሰብሳቢ ኮሎኔል ዐወል አብዱራሂም “ክለቦች ራሳቸው የሚመሩት የሊግ ኮሚቴ እንዲቋቋም በእኛ በኩል ቆርጠን ገብተናል። ክለቦች በሞግዚት መመራት የለባቸውም፤ ለእግርኳሱም እድገት ከዚህ ውጭ ሌላ አማራጭ የለም” ብለዋል፡፡

ለዚህ የሚሆን አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎች አጠናቀናል ያሉት ኮሎኔል ዐወል በዚህም ‹‹ጥር 7/2011 ዓ/ም ሁሉም የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ክለቦች አንድ ተወካይ መርጠው በመላክ 16 አባላት ያሉበት የኢትዮጵያ የሊግ ኩባንያ (PLC) ለመመስረት ትልቅ የመሰረት ድንጋይ የሚጣልበት ቀን ይሆናል፤ ይህ ለኢትዮጵያ እግርኳስም ትልቅ የመስራች ነው›› ብለዋል።

የሊግ አስተዳደሩ በተለያዩ ጊዜያት ይቋቋማል ተብሎ ሲነገር ቢቆይም ክለቦች ሳይስማሙ በልዩነት እየወጡ ሳይሳካ ቀርቷል። የዚህ የሊግ የማስተዳደር ዕጣ ፈንታንም ሁሉም በጉጉት የሚጠብቀው ጉዳይ ነው።

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami