በኢትዮጵያ ተገንብተው ወደ ስራ ከገቡት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ምርቶችን ወደ ውጭ በመላክ በአምስት ወር ውስጥ 55 ሚልዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ገልጽዋል፡፡
የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ መኮንን ሃይሉ ለኢቢሲ እንደገለጹት የመቐለ፣ ቦሌ ለሚ ፣ኢስተርን ኢንዱስትሪ፣ ጆርጅ ሹ ፣ ኮምቦልቻ፣ ሃዋሳ ፣ ዩጃን ፣ ቬሎሲቲ እና የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ያመረቱትን ምርት ወደ ውጭ መላክ ጀምረዋል፡፡
የኢንዱስትሪ ፓርኮቹ ለሃገሪቱ የውጭ ምንዛሬ ከማመንጨታቸውም በላይ በሺዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች የስራ አድል ፈጥረዋል፡፡
በኢንዱስትሪ ፓርኮቹ የአንድ መስኮት ማዕከል አገልግሎት በመጀመሩ የባለሃብቱን ግዜ እና ገንዘብ መቆጠብ መቻሉን አቶ መኮንን አብራርተዋል፡፡