የአፍሪካ መሪዎች በአዲሱ ዓመት ለህዝባቸው መልካም ነገር ለመስራት እየማሉ ነው
ብዙዎቹ አፍርሪካዊያን መሪዎች አዲሱን ዓመት ሲቀበሉ ህዝባቸው የተሸለ አስተዳደር እንደሚገባው በመግለፅ እና ያን ለማድረግ ከወዲሁ ቆርጠው መነሳታቸውን ደጋገመው ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡
የቻዱ ፕሬዝዳንት ኢድሪስ ዲቤይ የተራዘመውን የፓርላማ እና የአካባቢ ምርጫ በአዲሱ ዓመት መጀመሪያ ላይ በአስቸኳይ ለማካሄድ እና ህዝቡ የሚበጀውን እንዲመርጥ መደላድል ለመፍጠር ቃል ገብተዋል፡፡
በ2019 ኬንያ፣ ታንዛኒያ፣ ሩዋንዳ፣ ብሩንዲ እና ደቡብ ሱዳን የምስራቅ አፍሪካን ህብረት ይመሰረታሉ፣ ከምስራቅና ደቡብ አፍሪካ የጋራ ገበያ ከኮሜሳ ጋር በመተባበርም የአፍሪካን የጋራ ገበያ እንፈጥራለን ያሉት ደግሞ የታንዛኒያው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ናቸው፡፡
ሙሴቬኒ ወጣቶችን በማጠናከርና የሥራ እድል በመፍጠር ወንጀልን ማጥፋት አለብን ፣ይህን ስናደርግ ነው ወጣቱ ሀገሩን የሚገነባው በማለት የመጭው ዘመን እቅዳቸውን ተናግረል፡፡
ፕሬዝዳንት ሲርል ራፋሞሳ ደግሞ ሀላፊነት የሚሰማው ዜጋ ሁሉ በመጭው ምርጫ በመሳተፍ ለታላቋ ደቡብ አፍሪካ የሚመጥን መሪ በመምረጥ በመብቱን መጠቀም አለበት የሚል ጥሪ አስተላለፈዋል፡፡
በእንግሊዝኛ እና ፈረንሳይኛ ተናጋሪዎች መካከል ጎራ ፈጥረው እንገነጠላለን እያሉ የህዝቡን ላም የሚነሱት ሀይሎች ጋር ለመደራደርና የጋራ መፍትሄ ለማምጣት ዝግጁ ነኝ ያሉት የካሜሮኑ ፕሬዝዳንት ፓውል ቢያም ለህዝባቸው ደግ ደጉን ተመኝተዋል፡፡