የጉጂ ኦሮሞ አባ ገዳዎች የሰላም ሳምንት አወጁ
የጉጂ ኦሮሞ አባ ገዳዎች እስከመጪው እሁድ ጥር 5 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ የሰላም ሳምንት ማወጃቸው ተነግሯል።
በዚህ የሰላም ሳምንት ወቅትም የሰላም እና የመቻቻል የውይይት መድረኮችን ጨምሮ የተለያዩ መርሃ ግብሮች የሚካሄዱ መሆኑንም ነው ያስታወቁት።
በኢትዮጵያ መረጋጋት እና ዘላቂነት ያለው ሰላም እንዲሰፈን የበኩላቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውንም ነው የጉጂ ኦሮሞ አባ ገዳዎች ያስታወቁት።ኤፍቢሲ እንደዘገበው።