Uncategorized

ሂትሮው አየርመንገድ በድሮን ምክንያት በረራ አቋርጦ ነበር

ሂትሮው አየርመንገድ በድሮን ምክንያት በረራ አቋርጦ ነበር

በምእራብ ለንደን በሚገኘው የሂትሮው አየር መንገድ አቅራቢያ ድሮን በመታየቱ  ለሰዓታት በረራ እንዲቋረጥ እና መንገደኞች ባሉበት እዲቆዩ ተደርጎ ነበር፡፡

የአየር መነገዱ ቃል አቀባይ  ከፖሊስ እና ከደህንነት አካላት ጋር  ሁኔታውን እያጠኑት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ቢቢሲ እንደዘገበው መንገደኞቹ ከደህንነት ጋር በተያያዘ ምክንያት ከበረራቸው እንዲዘገዩ ሲነገራቸው የመደናገጥ ስሜት ተፈጥሮባቸው ነበር ፡፡

በወቅቱ በረራው እንዲቋረጥ የተደረገው ምላልባትም ነገሩ ከሽብር ጋር የተያያ ሊሆን ይችላል የሚል ስጋት በመፈጠሩ እንደነበር የአየር መንገዱ ቃል አቀባይ ገልፀዋል፡፡

ከአሁን ቀደም እዛው እንግሊዝ ውስጥ ጋትዊክ በተባለ አየር መንገድ ተመሳሳይ ክስተት በማጋጠሙ 140 ሺህ መንገደኞች ለ36 ሰዓታት ይህል ከጉዟቸው ተስተጓጉለው ነበር፡፡

በአሁኑ ጊዜ ፖሊስ እና የደህንነት ሰዎች ጉዳዩን በጋራ እየመረመሩት እንደሆነ እና መንገደኞች በሰላም ወደየመዳረሻቸው መሄዳቸውን ቃል አቀባይዋ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡

መንገደኞቹን በሙሉ ይቅርታ የጠየቀው  የሂትሮው አየር መንገድ እርምጃውን የወሰድነው ለደንበኞቻችን ደህንነት ቅድሚያ ለመስጠት መሆኑን እንደምትረዱን ተስፋ አለን ብሏል፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami