በኮንጎ ታሪክ የመጀመሪያው ተቃዋሚ ፕረዝዳንት ሆነው ተመረጡ
የጆሴፍ ካቢላ መንግስት ከአንድ የፖለቲካ ፓርቲ ጋር ስልጣን ለመጋራት ድርድር ላይ ነው በተሰማ ወሬ ከምርጫ ውጤት በኋላ ብጥብጥ እንዳይነሳ ስጋትን ፈጥሮ ነበር፡፡
በዚህም የተነሳ በኮንጎ የምርጫ ውጤት በሚገለፅበት ዋዜማ አድማ በታኝ ፖሊሶች በተጠንቀቅ ላይ ነበሩ፡፡
ዛሬ ማለዳ ይፋ በሆነው የምርጫ ውጤት ተቃዋሚው ፌሊክስ ሲሴኪንዲ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ለመሆን የሚያስችላቸውን ድምፅ በማግኘ አሸናፊናታቸው ታውቋል፡፡
ከተቃዋሚ ፓርቲዎቹ መካከል ለአሸናፊነት ትልቅ ግምት ተሰጥቷቸው የነበሩት ማርቲን ፋዩሉ ግን ውጤቱን ውድቅ አድርገውታል፡፡
ሲሴኪንዲ ከ7 ሚሊዮን በላይ ድምፅ ሲያገኙ ፋዩሉ ከ6.4 ሚሊዮን ያልዘለለ ድምፅ ነው ያገኙት ተብሏል፡፡
የፕሬዝዳንት ጆሴፍ ካቢላን ፓርቲ ወክለው የተወዳደሩት ኢማኑኤል ራማዛኒ ሻዳሪ ደግሞ ያገኙት ድምፅ አምስት ሚሊዮን አይሞላም፡፡
አንዳንድ የምርጫ ታዛቢዎች የምርጫ ሂደቱ በርካታ እንከኖች ታይተውበታው እንደነበር ከውጤቱ ቀደም ብለው አመላክተዋል፡፡
ለአብነትም አንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች ዘግይተው መከፈታቸው እና ቀድመው መዘጋታቸው እንዲሁም የምርጫውን ውጤት የሚቆጣጠሩ ማሺኖች የማይሰሩባቸው ጣቢያዎችም ነበሩ ብለዋል በሪፖርታቸው፡፡
ዲሞክራቲክ ኮንጎ ከ59 ዓመት በኋላ የመጀመሪያውን ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ብታካሂድም ውጤቱ በካቢላ መንግስት እና በአሸናፊው ጋት የሲሴኪንዲ ፓርቲ መካከል አሻጥር ሳይኖርበት አይቀርም የሚል ስጋት አማሳደሩ አልቀረም፡፡