EthiopiaLegal

የታራሚዎች ሰብአዊ መብት አያያዝ ለውጥ ማሳየቱን የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር አስታወቀ

የታራሚዎች ሰብአዊ መብት አያያዝ ለውጥ ማሳየቱን የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር አስታወቀ

ባለፉት ስድስት ወራት የታራሚዎች ሰብአዊ መብት አያያዝ ለውጥ ማሳየቱን የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር አስታወቀ።

የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር  አቶ ጀማል አባሶ የስድስት ወራት የስራ አፈፃፀሙን በማስመልከት ለመገናኛ ብዙሃን  በሰጡተ መግለጫ እንደተናገሩት፥በባለፉት 6 ወራት የታራሚዎች የሰብአዊ መብት አያያዝ እና ተቋማዊ መዋቅሩ መሻሻል አሳይቷል።

በታራሚዎች እና በጥበቃ አባላት መካከል የነበሩ አለመግባባቶችን ወደ መልካም ግንኙነት ከመቀየር አንስቶ እስከ ከፍተኛ አመራሩ የስነ ምግባር ለውጥ ለመፍጠር ያስቻሉ ስልጠናዎች መሰጠታቸውንም አመላክተዋል።

በሌላ በኩል የተቋሙን የፍትህ ስርአት ከማሻሻል አኳያ ከላይ እስከ ታች በ103 አመራር ላይ የመተካካት ስራ መሰራቱን ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።

የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር መመስረቻ አዋጅን ጨምሮ 34 የተለያዩ አዋጆች፣ መመሪያ እና ደንቦች ላይም ጥናት የተካሄደ ሲሆን፥ በቅርቡ ይፀድቃሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም አቶ ጀማል ጠቅሰዋል።

 

 

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami