ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ወደ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ሴራሊዮን አቀኑ
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሴራሊዮን ጉብኝታቸውን የሚያደርጉት ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ቀናት ነው።
ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚጠቁመው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝቱን የሚያካሂዱት ከሴራሊዮን ፕሬዚዳንት ጁልየስ ማዳቢዩ በተደረገላቸው ግብዣ መሰረት ነው ተብሏል።
በጉብኝቱ ወቅት ሁለቱ ባለስልጣናት የሴራሊዮን እና ኢትዮጵያን ወዳጅነት ሊያጠናክር የሚችል ምክክር በማድረግ የመግባቢያ ስምምነት ይፈራረማሉ ተብሎ ይጠበቃል።