Politics

የአማራ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ስራአስፈፃሚ ኮሚቴ ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ ከተማ ሲያካሂድ የቆየውን ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ አጠናቋል

የአማራ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ስራአስፈፃሚ ኮሚቴ ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ ከተማ ሲያካሂድ የቆየውን ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ አጠናቋል

ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በክልሉ የህግ የበላይነት ተረጋግጦ ሰላምና መረጋጋት በማስፈን በኩል መሰራት አለባቸው ተብሎ የተማነባቸውን ጉዳዮች በመወያየት ውሳኔ ማሳለፉን የማዕከላዊ ኮሚቴው ፅህፈት ቤት አስታውቋል።

ከዚህ በተጨማሪም ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር እንዴት በጋራ መስራት እንደሚቻል በዝርዝር በመወያየት አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡

ስራ አስፈፃሚው እንደሀገር ሰላምና መረጋጋት በሚፈጠርባቸው ጉዳዮች ላይም ፓርቲው ያለውን አሰተዋፅኦ አጠናከሮ ስለሚቀጥልበት ሁኔታም መክሯል ተብሏል፡፡

በክልሉ ህዝቦች ላይ የሚስተዋለው የመፈናቀል ችግር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ለመፍታት የሚያስችል አቅጣጫ ማስቀመጡንም አማራ ብዙሃን መገናኛ ዘግቧል፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami