የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን ሊያካሂድ ነው
የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከመጭው ሰኞ ጀምሮ መደበኛ ስብሰባውን እንደሚያካሂድ ገለጸ፡፡
ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በስብሰባው በ11ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ የተቀመጡ አቅጣጫዎች አፈጻጸም ላይ ውይይት ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።
ከአፈጻጸም ግምገማ በተጫማሪም በሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ እና የለውጥ እንቅስቃሴ ሂደት ላይ ይመክራልም ተብሏል፡፡
እንዲሁም የድርጅት እና የመንግስት የስራ አፈጻጸም ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ ተወያይቶ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል፡፡ መረጃውን ያገኘነው ከድርጅቱ ገጽ ነው፡፡