የገቢዎች ሚኒስቴር በታህሳስ ወር ከሀገር ውስጥ ታክስ 8.5 ቢሊየን ብር ሰበሰብኩ አለ።
የገቢዎች ሚኒስቴር በታህሳስ ወር ከሀገር ውስጥ ታክስ ለመሰብሰበሰ ካቀደው 10ነጥብ 2 ቢሊየን ብር 8 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር የሰበሰበ ሲሆን ፤አፈፃፀሙም 83ነጥብ 5 በመቶ መሆኑን የሚኒስቴር መ/ቤቱ የሀገር ውስጥ ታክስ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ መሀመድ አብዱ ገልፀዋል፡፡
እንደ አቶ መሀመድ ገለፃ ለዕቅዱ አለመሳካት በዋናነት የሰራተኛ ድልድል በተፈለገው ፍጥነት አለመጠናቀቅ፤የታክስ ውሳኔ ቅሬታ አፈታት ቀልጣፋ አለመሆን፤በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በኩል በወሩ የታዩ ክፍተቶች ሲሆኑ ደረሰኝ ያለመቁረጥ ፣በተደጋጋሚ ባዶ ወይም ኪሳራ ማሳወቅ እና ግብርን በወቅቱ አስታውቆ አለመክፈል ደግሞ በግብር ከፋዩ በኩል በወሩ የነበሩ ተግዳሮቶች ናቸው ብለዋል ፡፡
በመጨረሻም በቀጣይ እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ እንዲሁም የገቢ እቅዱን ለማሳካት በደረሰኝ አና በተጨማሪ እሴት ታክስ ዙሪያ አተኩሮ መስራት፣የኢ-ፔይመንት ስራዎችን አጠናክሮ መቀጠል፣ የሰራተኞች የስራ ተነሳሽነት እንዲዳብር ማድረግ፣የቅሬታ አፈታት ስረዓቱን ማሻሻልና ቀልጣፋ የማድረግ ስራ እንደሚሰራ አቶ መሀመድ ገልፀዋል፡፡
ምንጭ ፦ገቢዎች ሚኒስቴር