የIAAF ወኪል ኢትዮጵያን ጎብኝተዋል
የIAAF ወኪል ሚ/ር ጂ ኢሥራም ዛሬ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ቢሮ በመገኘት የሥራ ጉብኝት አድርገዋል። በጉብኝታቸው ወቅት የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ኮሎኔል አትሌት ደራርቱ ቱሉ ፣ የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ቢልልኝ መቆያና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች በአጠቃላይ የተቋሙ እንቅስቃሴ ገልፃ ተደርጓል። በገለፃው ሚ/ር ጂ ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል።
በተያያዘ መረጃ…
ከቀናት በፊት የምሥራቅ አፍሪካ አትሌቲክስ ሪጅን ኮንግረስ ስብሰባ በአዲስ አበባ ጥር 4/2011 ዓ.ም በካፒታል ሆቴል ተካሂዷል።
በዕለቱ የምሥራቅ አፍሪካ አትሌቲክስ ሪጅን የቦርድ አባላት ምርጫ ተካሂዶ ኮሎኔል አትሌት ደራርቱ ቱሉ ም/ፕሬዝዳንት ሆና በሙሉ ድምፅ ተመርጣለች።
በተጨማሪም ኮሎኔል ደራርቱ በአፍሪካ አትሌቲክስ ኮንፌዴሬሽን /CAA/ ውስጥ ሪጅኑን በመወከል የቦርድ አባል ሆና ተመርጣለች።