Uncategorized

ባለሀብቶች የግብርና ምርቶችን የሚሰበስብ የሰው ኃይል አጣን አሉ፣ ምክንያቱ ደግሞ የፀጥታ ችግር ነው ብለዋል።

ሰፋፊ እርሻዎች ባሉባቸው አካባቢዎች በየጊዜው እያጋጠመ ያለው የፀጥታ መደፍረስ በፈጠረው ሥጋት፣ ባለሀብቶች የግብርና ምርቶችን የሚሰበስብ የሰው ኃይል ማግኘት አልቻልንም እያሉ ነው፡፡

በተለይ በአማራ፣ በቤኒሻንጉል ጉምዝ፣ በጋምቤላና በአፋር ክልሎች ምርት መሰብሰብ በነበረበት ጊዜ እያጋጠመ ያለው ግጭት፣ የሰው ኃይል ወደ ሥፍራው እንዳይንቀሳቀስ አድርጓል  ነው ያሉት ባለሀብቶቹ፡፡

የኢትዮጵያ ጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የጥጥ ዘርፍ ምክትል ዳይሬክተር አቶ መሰለ መኩሪያ እንደገለጹት፣ በተለይ በአማራ ክልል መተማ አካባቢ መንገድ በመዘጋቱ ጥጥና ሰሊጥ የሚሰበስቡ ሠራተኞችን ማግኘት አልተቻለም፡፡

ሪፖርተር እንዳስነበበው ምርት በሚሰበሰብበት በዚህ ጊዜ አንድ እርሻ ብቻ ከ2 ሺህ እስከ  3 ሺህ ሠራተኞች ይፈልጋል ተብሏል፡፡

በዚህ ዓመት ለኢትዮጵያ ጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ 58 ሺሕ ሜትሪክ ቶን የተዳመጠ ጥጥ ይገኛል ተብሎ ታቅዶ ነበር፡፡ ጥጥ ከእርሻ ላይ በወቅቱ የሚነሳበት ዕድል በመጥበቡና ከሚቀጥለው ወር በኋላ ዝናብ ይጥላል ተብሎ ስለሚገመት፣ የምርት ውድመት ያጋጥማል ተብሎ ተሠግቷል፡፡

 

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami